Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ሥርዓትን ተግባራዊ  በማድረግ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ ይገባል -የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረብሄራዊ የፌደራል ሥርዓትን ተግባራዊ  በማድረግ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ እንደሚገባ የፌደሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡

በሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፍፃፀም ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በ2015 በጀት በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ አበረታች ሥራዎች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሕገ መንግሥትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ዙሪያ የሚሠሩ ሥራዎች በቂ እንዳልሆኑ በመጥቀስ  በቀጣይም  ትኩረት ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

ኅብረብሄራዊ የፌደራል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን መቅረፍ እንደሚገባ ጠቁመው÷ በሕገ መንግሥቱ  እና ፌደራል ሥርዓቱ አስተሳሰቡ የዳበረ ማህበረሰብ መፍጠር  እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይም የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ የአስተምህሮ ማዕከሉ ከምክር ቤቱ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የተጣለበትን ኃላፊነት መወጣት አለበት ማለታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.