Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በተካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ላይ ተሳተፉ

ጠ/ሚ ዐቢይ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በተካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሞቃዲሾ በተካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ ማህሙድ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጊሌ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ነው ሽብርተኝነትን በመዋጋት ዙሪያ የመከሩት፡፡

መሪዎቹ በውይይታቸው፥ አሸባሪውን አልሸባብ ከቀጣናው ለማጥፋት ከዚህ ቀደም በበለጠ ትብብር ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪውን አልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቀጣናውን ሀገራት ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ጥላ ስር ተሰማርቶ አልሸባብን እየተዋጋ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዦች ጋርም ተወያይተዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሶማሊያ በተካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ሞቃዲሾ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.