Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2023ቱ የለንደን ማራቶን ይሳተፋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቀጣይ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ ተገለፀ፡፡

ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን 2 ሰአት ከ1 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛው የፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል ።

የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ22 ደቂቃ በመግባት ቀደም ብሎ በእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ተይዞ የነበረውን የለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን ማሻሻሉ ይታወሳል።

ሞስነት ገረመው ፣ ብርሀኑ ለገሰ  እና ልዑል ገብረስላሴ  በውድድሩ  ኢትዮጵያን  ሚወክሉ  አትሌቶች ናቸው ተብሏል።

የ2022 የለንደን ማራቶን አሸናፊው ኬኒያዊው አሞስ ኪፕሩቶ እና እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ በዚህ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ መባሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.