Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሩሲያ አምባሳደርና ከአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጌኒ ተርኪን እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ጋር ትሬሲ ጃኮብሰን እና ጋር መክረዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ ፥ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን ታሪካዊና ወዳጃዊ ግንኙነት እንደምታደንቅ ገልጸው ፤ የሀገራቱን ሁለትዮሽ ትብብርን በተለያዩ ዘርፎች ማስፋፋት ያለውን ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ ሁለቱ ወገኖች የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነቶች አተገባበር እንዲሁም የሁለትዮሽ ስምምነቶቻቸውን በተለያዩ ዘርፎች በንቃት የመከታተል አስፈላጊነት ላይም መክረዋል።

በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል የተካሄደውን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ እንደገና ለማነቃቃት በሚወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም በመጪው 2ኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይም እንዲሁ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ የአሜሪካን ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ጋር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር ባደረጉት ውይይት ፥ የኢትዮ- አሜሪካ ወዳጅነት ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለተከናወነው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ ላደረገችው ድጋፍም አመስግነዋል።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ለአምባሳደሯ ገልጸው ፥ አሜሪካም ለሚደረገው የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ስራ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በሽግግር ፍትህ ስርዓት መሰረት ለመፍታት ቁርጠኝነት መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ላይ የሰሯቸው ፖለቲካዊ አድሏዊነት የተጫነው በመሆኑ አሜሪካን ውድቅ እንድታደርገውም ነው የጠየቁት።

አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በበኩላቸው ፥ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የተተገበረውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለይም የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽነት በአስደናቂ ሁኔታ መጨመሩን፣ የጦርነቱ መቆም፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቶች መከፈታቸውና በሽግግር የፍትህ ስርዓት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.