Fana: At a Speed of Life!

የእድሜ ተገቢነት እርምጃው ቀጥሏል- ፌዴሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌቶች እድሜ ተገቢነት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

በአሰላ አረንጓዴው ስቴዲየም ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና  እየተካሄደ እንደሚገኝ የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሻምፒዮና ውድድሩ ከ250 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች ከተፈቀደው የእድሜ ገደብ ውጭ ሲሳተፉ እንደነበር ፌደሬሽኑ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በዚህም  ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከእድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ ተረጋግጦ ፌዴሬሽኑ ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ተግባሩን በፈፀሙ ቡድኖችና አሰልጣኞች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለየክልላቸው፣ ከተማ አስተዳደራቸው፣ ክለባቸውና ተቋሞቻቸው ማስጠንቀቂያ የሚላክ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በአትሌቶች ላይ በሚደረገው ምርመራ ተጨማሪ መረጃ ከተገኘ አትሌቶቹ  የተሸለሙትን  ሜዳልያም ሆነ የገንዘብ ሽልማት  ለፌደሬሽኑ ተመላሽ እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.