Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ከዕረፍት መልስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ተሳትፎ እና ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ ከ40 ቀናት በኋላ ይመለሳል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት በ12ኛ ሳምንት የሊጉ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ በእግር ኳስ ቤተሰቡ በጉጉት የሚጠበቅ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ ለ45ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ 21 ጊዜ ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 7 ጊዜ አሸንፏል፤16 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ፈረሰኞቹ ባደረጓቸው የባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሶስት ጊዜ ሲያሸንፉ ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል።

ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ደግሞ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.