Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲን የሚወክሉ የምክር ቤት አባላትና የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት አመራሮች በመንግስት የስድስት ወር አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮች በመንግስት የስድስት ወር አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ጀመሩ።

መድረኩን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ያስጀመሩት ሲሆን፥ ውይይቱ ፓርቲው በምርጫ ወቅት በማኒፌስቶው ያስቀመጣቸው እና ለሕዝብ ቃል የገባቸው ጉዳዮች አፈፃፀምን ይመለከታል።

የውይይት መድረኩ፥ የእነዚህን ተግባራት የአፈፃፀም ደረጃን በመለየት በቀጣይ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ የክትትልና ድጋፍ ሥራ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያግዛልም ተብሏል።

የመንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርት በኘላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ እየቀረበ ይገኛል።

በውይይቱ ባለፉት ስድስት ወራት በተከናወኑ ተግባራት ላይ ዝርዝር ውይይት ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልፅግና ፅህፈት ቤት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.