Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በቱርክ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ የተመራው ወታደራዊ የልዑካን ቡድን በቱርክ ጉብኝት አደረገ፡፡

ልዑኩ የቱርክ ወታደራዊ ኃይል በክረምት ወቅት የተጣለበትን አገራዊ እና ዓለም-አቀፋዊ ግዳጅ ለመወጣት ያለዉን አቅምና ዝግጁነት ለማሳየት ጥር 24 እና 25 ቀን 2015 ዓ.ም በምስራቅ ቱርክ ካርስ ግዛት በተዘጋጀው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተሳትፏል፡፡

እንዲሁም የልዑካን ቡድኑ የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ዘርፍ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.