Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  በሠላምና ጸጥታ ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  በሠላምና ጸጥታ ዘርፍ በተቀናጀ መንገድ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት ተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል።

የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት በክልሉ ባለፉት 6 ወራት የተከናወኑ የሠላምና የጸጥታ ሥራዎችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ገምግሟል።

በግምገማውም÷ በክልሉ በሠላምና ጸጥታ ዘርፍ በተቀናጀ መንገድ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል።

ሠላምን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ከሚገኙ ሥራዎች ጎን ለጎን ዜጎችን መልሶ የማቋቋም እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

የሕዝቡን አብሮነት የበለጠ ለማጠናከር እና ሠላሙን ዘላቂ በማድረግ በኩል የበኩሉን እንዲወጣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች  እተከናወኑ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

የጸጥታ ምክርቤቱ በክልሉ በቀጣይ ዘላቂ ሠላምን በማረጋገጥ በሙሉ አቅም ወደልማት ለመግባት የተጀመሩ የሠላምና ጸጥታ ሥራዎችን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.