Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ጥሬ ገንዘብ ወደ መቀሌ መላክ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ውሳኔን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ጥሬ ገንዘብ ወደ መቀሌ መላክ ጀመረ።

ጥሬ ገንዘቡ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መሠራጨት እንደሚጀምር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታውቀዋል።

 

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድም ወደ መቀሌ የሚያደረገውን ዕለታዊ በረራ ቁጥሩን ከሶስት ወደ አምስት ማሳደጉን አምባሳደር ሬድዋን ገልፀዋል።

የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በትናንትናው ዕለት በሐላላ ኬላ ተገናኝተው ምክክር ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዲጨምሩ፣ የባንክ አገልግሎት እንዲፋጠን እና ሌሎች እርስ በርስ መተማመንን የሚያጎለብቱ እና የዜጎችን አኗኗር የሚያቀሉ አገልግሎቶች እንዲፋጠኑም መመሪያ ማስተላለፋቸውም ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.