Fana: At a Speed of Life!

ህዝበ ውሳኔው በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን የወላይታ ዞን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የወላይታ ዞን አስተዳደር አስታውቋል፡፡
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በነገው ዕለት የሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ይካሔዳል።
ህዝበ ውሳኔው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻልም በወላይታ ዞን የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ 8 የምርጫ ማዕከላት እና 1ሺህ 112 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ያነሱት አቶ አክሊሉ÷የጸጥታ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የምርጫ ቁሳቁስ ያለምንም ችግር ወደ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መሰራጨቱን ጠቁመዋል።
በህዝብ ውሳኔ ቀንም ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት ዝግጁ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል፡፡
ሕዝብ ውሳኔው ነገ ጠዋት ከ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት እንደሚካሄድ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መርሐ ግብር ያሳያል፡፡
በጥላሁን ሁሴን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.