Fana: At a Speed of Life!

የ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች የተሳተፉበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ በሁለቱም ጾታ በ218 ነጥብ 1ኛ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል ደግሞ በ213 ነጥብ 2ኛ እና በ210 ነጥብ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ሦስተኛ በመሆን የአጠቃላይ አሸናፊነት ደረጃን ይዘዋል፡፡

በሴቶች አጠቃላይ አሸናፊ÷ በ132 ነጥብ 1ኛና የዋንጫ ተሸላሚ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በ98 ነጥብ 5 ነጥብ 2ኛ የገንዘብ ተሸላሚ ኦሮሚያ ክልል እና በ78 ነጥብ 3ኛ የገንዘብ ተሸላሚ መቻል ሆነዋል፡፡

በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊ÷ በ138 ነጥብ 1ኛና የዋንጫ ተሸላሚ ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል፣ በ111 ነጥብ 5 ነጥብ 2ኛና የገንዘብ ተሸላሚ ኦሮሚያ ክልል እና በ86 ነጥብ 3ኛና የገንዘብ ተሸላሚ የኢትዮጵያ ንግድባንክ መሆናቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.