Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በጎ አድራጊዎችን በማሳተፍ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሰው ተኮር ተግባራትን ለወገኖቻችን ማድረሳችንን፣ አዲስ አበባን ደሃና ሃብታም በሚዛናዊነት የሚኖርባት የምትመች ማድረጋችንን ቀጥለናል ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የሕዝብን ጥያቄ የሚመልሱ ናቸው መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል÷ በመዲናዋ 14 ኛው እና እስከ 1 ሺህ 200 በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ወገኖች የሚመገቡበት ማዕከል እንዲሁም በቀን 600 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለውና ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የሚፈጥረው ሳሪድ ዳቦ ፋብሪካ ይገኙበታል።

በተጨማሪም አዲስ የተገነቡ የመማር ማስተማሩን ሂደት ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የሁለተኛ እና የቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 60 የመማሪያ ክፍሎች እንዲሁም 120 ሱቆች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.