Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኮቪድ-19 ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለሚያስከትለው ቀውስ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት ስለማጠናከር መወያየታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይቱ ከኢኮኖሚ ጉዳት ለማገገም በምንሠራበት በዚህ ወቅት መሆኑ መልካም ነው ብለዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ በዓለም ባንክ እና በጂ20 አማካኝነት ለአፍሪካ የሚቀርበውን ድጋፍ በዋናነት ከሚያስተባብሩት ፕሬዚደንት ፑቲን ጋር ውይይት በማካሄዳቸው ደስተኛ መሆናቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.