Fana: At a Speed of Life!

በግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት 99 በመቶ ወደ አገልግሎት ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኃይል አቅርቦት 99 በመቶ ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉን አስታወቀ።

ስምንት የ230 ኪሎ ቮልት እና አምስት የ132 ኪሎ ቮልት አቅም ያላቸው ማከፋፈያ ጣቢያዎች ተጠግነው አገልግሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

1 ሺህ 561 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የ230 እና 132 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተደርጎ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑም ነው የተነገረው።

ተቋሙ ሥራውን ያከናወነው በሰሜን ምሥራቅ በኩል፥ ኮምቦልቻ – ወልዲያ- አላማጣ እና በሰሜን ምዕራብ ወልቃይት – ሑመራ – ሽረ መስመሮች ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የዶሮ ግብር የማከፋፈያ ጣቢያ ከተንቀሳቃሽ ወደ ቋሚ ማከፋፈያ ጣቢያ መቀየሩ ተመላክቷል።

ቀሪው ወደ ጭፍራ፣ ሐራ ገበያ እና የተወሰኑ የአፋር አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ በሚያደርገው መስመር ላይ የሚከናወነው የመቆጣጠሪያ ሥራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ሥራውም በአንድ ሣምንት እንደሚጠናቀቅ ነው የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።

ቀሪውን ሥራ ሳይጨምር ለጥገና ሥራው ከ328 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል ነው ያሉት።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.