Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ አልሚዎች ድጋፍ እንደሚደረግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፁ።

አቶ ኡሞድ በክልሉ በጎግ ወረዳ ኡበላ አካባቢ አንድ ባለሃብት እያከናወኑት ያለውን የልማት ሥራ ተመልክተዋል፡፡

ክልሉ ለእርሻ ልማት የሚመች ሰፊ ለም መሬት፣ የከርሰ ምድር እና የገፀ ምድር የውኃ ሃብት እንዳለው በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

ይህን ሃብት በአግባቡ በማልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ  ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.