Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተከማዋ ውስጥ የሚገኙ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት አሠራር ላይ የማሻሻያ ውሳኔዎች ማስተላለፋን ያስታወሰው የከተማ አስተዳደሩ።

በመሆኑም ውሳኔውን ተከትሎ በቂ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የሀገር አቋራጭ አውቶቢስ ባለንብረቶች በሙሉ መሣተፍ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ነው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለከተው።

ፍላጎት ያላቸው የአውቶቡስ ባለንብረቶች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን በግንባር በመምጣት ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ስምሪት ወስደው ወደ ስራ እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.