Fana: At a Speed of Life!

ከኢኮኖሚ፣ ከታክስና ጉምሩክ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ከ1 ሺህ በላይ መዝገቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢኮኖሚ፣ከታክስና ጉምሩክ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ባለፉት ስድስት ወራት በ1 ሺህ 380 መዝገቦች ላይ ክስ መመስረቱን ፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፍርዴ ቸሩ እንደገለጹት÷ከታክስና ጉምሩክ እንዲሁም ከሸማቾችና ከልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ጋር ተያያዞ በ6 ወራት በ1 ሺህ 380 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

በዚህ የክስ ሂደት በ276 መዝገቦች 497 ተከሳሾች እንደ ክስ አመሰራረት ሂደቱ ወንጀሉን በመፈጸማቸው በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ፍርድ እንደተላለፈባቸው ተናግረዋል፡፡

በ15 መዝገቦች 25 ተከሳሾች በነጻ ተሰናብተው 1 ሺህ 100 መዝገቦች በክርክር ሂደት ላይ መሆናቸውንም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡

ተቋሙ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጠር የኢኮኖሚ አሻጥርን በመከላከል፣ የንግዱ ማህበረሰብ የሸማቹን መብት ያከበረ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲያደርግና ይህንን ተላልፎ ሲገኝም በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.