Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ15 ሚሊየን ዶላር የተገዙ የፍሳሽ ማንሻ ተሽከርካሪዎችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለስልጣኑ የፍሳሽ ቆሻሻ የማንሳት አገልግሎቱን የላቀ ለማድረግ ከዓለም ባንክ በተገኘ 15 ሚሊየን ዶላር ብድር የገዛቸውን 90 የፍሳሽ ማንሻ ተሽከርካሪዎች ተረከቧል፡፡

የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰርካለም ጌታቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ተሽከርካሪዎቹ ዘመናዊ የፍሳሽ በመስመር ማስወገድ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ተሸከርካሪዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት በተካሄደ ስልጠና ላይ እንደተናገሩት÷ ተሽከርካሪዎቹ የሚነሳውን የፍሳሽ መጠን ከማሳደግ ጎን ለጎን በወረፋ ምክንያት ያልተስተናገዱ ደንበኞችን ችግር ይቀርፋሉ፡፡

ባለሙያዎችም ተሽከርካሪዎቹ ያለ ችግር ረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.