Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለኮቪድ-19 መከላከል ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 29፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

ለኮሮና ቫይረስ ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማሰባሰብ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በዛሬው እለት የተለያዩ ድርጅቶች ለብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ድጋፍ አድርገዋል።

በዚህም ዘመን ባንክ 5 ሚሊዮን ብር፣ ረፒ ዲተርጀንት 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር፣ አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ኒያላ ሞተርስ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ጊፍት ሪልኢስቴት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ ኦሮሚያ ኢንሹራንስ 1 ሚሊየን ብር ፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት 650 ሺህ ብር፣ ኢቲዮ ታኮማል 500 ሺህ ብር እና የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማህበር 100 ሺህ ብር ለግሰዋል።

የብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ድርጅቶቹ በዚህ ክፉ ሰዓት ከህዝብ ጎን ሆነው ህዝባዊ ወገተኝነታቸውን ላሳዩት ድርጅቶች ምስጋና ማቅረባቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሌላም በኩል በዛሬው እለት የተለያዩ ተቋሟትና ግለሰቦች ለአዲስ አበባ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የ11 ሚሊየን ብር ድጋፍ አበርክተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለውን ድጋፍ የማሰባሰብ ጥሪ ተከትሎ ድጋፉ መደረጉ ነው የተገለጸው።

በዚህም በዛሬው እለት ከእምነት ተቋማት ፣ ከድርጅቶች እና ግለሰቦች 6 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እና ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ ተሰብስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.