Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቱርክ እና ሶርያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ እና ሶርያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መግለጫ በደረሠው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱትም ብርታትን ተመኝተዋል።

በደቡባዊ ቱርክ እና በሰሜን ሶሪያ በደረሠው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ4 ሺህ 300 ሰው በላይ ህይወት አልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.