Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ ተገለፀ።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት አንቀጽ 57 ንጹስ አንቀጽ 3/1 እና የይቅርታ ደንብ 114/98 በሚያዘው መሰረት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲለቀቁ ወስነዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት መከላከልን ምክንያት አድርጎ ለታራሚዎች የተደረገው ይቅርታ የክልሉ ህገ መንግስት እና በይቅርታ ደንብ ለክልሉ ርእሰ መስተዳደር በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተወሰነ መሆኑም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.