Fana: At a Speed of Life!

የሕዝበ-ውሳኔው ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና አስተባባሪ መቅደስ መኮንን እንዳሉት÷ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቋል ።

ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጸዋል።

ህዝብ ውሳኔ በክልሉ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች ትናንት መካሄዱን አስታውሰዋል።

በየደረጃው የተሰማሩ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላት የምርጫውን ስነ-ስርዓት ለማስፈጸምበተቀናጀ መንገድ እንደተንቀሳቀሱ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.