Fana: At a Speed of Life!

በዓመቱ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀቱ ዓመቱ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው።

በግምገማው መሰረት የክልሉ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ሪፖርታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እያቀረቡ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ፥ ለህዝብ የገባናቸውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ስራዎች በተግባር ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በበጀቱ ዓመቱ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ አንፃርም እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።

መስተዳድር ምክር ቤቱ እያካሄደው የሚገኘው ግምገማ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.