Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ከ30 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 30 ሺህ 900 አዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት÷ በመዲናዋ የተሟላ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስጠት የሚችሉ 15 ኮሌጆች ሰልጣኞችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል።

እነዚህ ፖሊኮሌጆች ከ158 ሺህ በላይ የሙያ ሰልጣኞችን ማስተናገድ የሚችሉ ቢሆንም አሁን እየተቀበሉ ያሉት ከግማሽ በታች መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣይ የሰው ሃይልና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ታሳቢ በማድረግ የሰልጣኖችን ቅበላ ከፍ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 30 ሺህ 900 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.