Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና የ161 ሚሊየን ብር የአስቸኳይ ምግብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና የ161 ሚሊየን ብር የአስቸኳይ ምግብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና ንግድ አማካሪ ሚስተር ያንግ ዪሀንግ ተፈራርመውታል።

የፋይናንስ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚውል ሲሆን፥ በሀገሪቱ በግጭትና በተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

በስምምነቱ ወቅት በተካሄደው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚካሄደው የኢኮኖሚ ትብብር በቀጣይ የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ቻይና ለኢትዮጵያ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል መገለጹን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.