Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ19ን ፈተና ልንወጣ የምንችለው እንደ አንድ ተከላካይ ሠራዊት ስንቆምብቻ ነው­- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝን ፈተና ልንወጣ የምንችለው እንደ አንድ ተከላካይ ሠራዊት ስንቆምብቻ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር በዛሬው እለት በድጋሚ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በቀጣዮቹ ቀናት ኮቪድ19ን በተመለከተ የሚወሰዱ ተጨማሪ ርምጃዎችን በተመለከተ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አስታውቅዋል።

በዚህም “ኮቪድ19 የሚያስከትለው ቀውስ ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ እንደ መሆኑ፣ ፈተናውን ልንወጣው የምንችለው እንደ አንድ ተከላካይ ሠራዊት ስንቆምብቻ ነው” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.