Fana: At a Speed of Life!

ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በመጪው ቅዳሜ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በሚያደርጉት የሸገር ደርቢ ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ አክሲዮን ማህበር ከ14ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት እንዲሁም ሁለት ተስተካካይ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2015 ዓ.ም ጨዋታዎች ውድድር መርሃ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ለማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተስማምቶ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ሆኖም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ቅዳሜ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ውድድሩን በመርሃ ግብሩ መሰረት ማካሄድ አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም እና የደሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም በአማራጭነት አስቀምጦ ፤በመጨረሻም በተለያዩ ምክንያቶች በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታው እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.