Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች እና የልዑካን ቡድኖቻቸው በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ በባሕር፣ በሎጅስቲክስ እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ማሳደግን ጨምሮ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ ምክክር አካሂደዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች እርስ በእርሳቸው የሚማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ጠቅሰዋል።

አያይዘውም የዛሬው ውይይት የተለያዩ የትብብር መስኮችን ይበልጥ አጠናክሯቸዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ጠዋት በማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላ ይፋዊ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እንደተደረገላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.