Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የመንግስት የጋራ ጉባኤ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና በመንግስት መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተቋቁሟል።
ጉባኤው በዋናነት በፖሊሲና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የፌዴራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የመንግስት የትብብር መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ እንዳሉት÷የጋራ ጉባኤ መቋቋሙ ሁለቱም አካላት ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው ፡፡
የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ÷ዘላቂ ሰላም፣ አካታች ልማት፣ መልካም አስተዳደር እና ሰብዓዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ማስቻል የጋራ ጉባኤው የትኩረት መስኮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ መለሰ በበኩላቸው÷የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገለልተኛ የሆነ አቋማቸውን በመጠበቅ ለሀገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ከመንግስት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የመንግስት የጋራ ጉባኤ በክልሎች ደረጃ ከዚህ ቀደም ተቋቁሞ በተግባር ላይ ሲሆን÷ ዛሬ የተመሰረተው በፌደራል ደረጃ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.