Fana: At a Speed of Life!

ጋናዊው ተጫዋች ክርስቲያን አትሱ በቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍርስራሽ ስር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቼልሲና በኒውካስል ተጫውቶ ያሳለፈው ጋናዊው የመስመር አማካይ ክርስቲያን አትሱ በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የጉዳት ሰለባ ቢሆንም በህይወት መትረፉ ተሰምቷል።

ጋናዊው የመስመር አማካይ በቱርክ ከህንጻ ፍርስራሽ ስር በህይወት መገኘቱም ነው የተሰማው።

የቀድሞ የኒውካስትል፣ ቼልሲ እና ኤቨርተን ተጫዋች አሁንበየሚጫወትበት የቱርኩ ሃታያስፖር ክለብ ነው አደጋው ያጋጠመው።

የክለቡ መቀመጫ የሆነችው ሃታይ ከተማ ቱርክን በመታት ርዕደ መሬት ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱ ከተሞች መካከል አንደኛዋ ስትሆን በርካቶችም በፍርስራሽ ተቀብረው ቀርተዋል።

ተጫዋቹ እና የክለቡ ዳይሬክተር ታነር ሳቩት ከርዕደ መሬቱ በኋላ ጠፍተው እንደነበር ክለቡ ሲገልጽ ቆይቷል።

በተደረገው ፍለጋም አትሱ ፍርስራሽ ውስጥ ሲገኝ ዳይሬክተሩን የማፈላለጉ ስራ ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው።

አሁን ላይም በአደጋው ሳቢያ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ነው ብሏል የቱርኩ ክለብ ባወጣው መግለጫ።

አሁን ላይ ለቱርኩ ሃታያስፖር ክለብ የሚጫወተው ክርስቲያን አቱሱ ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ በኒውካስትል ዩናይትድ፣ ኤቨርተን እና ቼልሲ ተጫውቶ አሳልፏል።

ተጫዋቹ ባለፈው እሁድ ክለቡ በነበረው ጨዋታ የማሸነፊያዋን ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

ሃታይ ከተማ በርዕደ መሬቱ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደች ከተሞች ውስጥ አንዷ መሆኗም ነው የተገለጸው፡፡

በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ሶሪያ በተከሰተው ርዕደ መሬት ሳቢያ እስካሁን ከ4 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ደይሊ ሜይል በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.