Fana: At a Speed of Life!

በምርት ዘመኑ ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአኩሪ አተር ምርት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014/15 ምርት ዘመን ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአኩሪ አተር ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአኩሪ አተር ሰብል ልማትና ግብይት ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ በሚኒስቴሩ የእርሻና “ሆርቲካልቸር” ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን እንደተናገሩት ፥ ለውጭ ገበያና ለአምራች አንዱስትሪው የሚውል አኩሪ አተር በበቂ መጠን ማምረት የሚያስችል ምቹ ስነ-ምህዳር አለ፡፡

በሀገር ደረጃም በምርት ዘመኑ በአኩሪ አተር የለማው 340 ሺህ ሄክታር መሬት መሆኑን ጠቁመው ፥ ከዚህም ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል ነው ያሉት።

ሆኖም የተደራጀ የገበያ ሥርዓት ያለመፈጠር እንዲሁም በሥራ ላይ ያሉት የህግ ማእቀፎች፣ አዋጆችና ፖሊሲዎች ምቹ ያለመሆን አምራቹን ቀጥተኛ ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ክፍተቶች ያሉባቸው መሆኑን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.