Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ባለሀብቶችን ችግሮች መፍታት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ የውጭ ባለሀብቶች ችግሮችን በሚገባው መጠን መፍታት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ የፖሊሲ ምክክር በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል ።

በምክክሩ ላይ የተገኙት አቶ ደመቀ መኮንን ÷በሀገር ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ የውጭ ባለሀብቶች ችግሮች በሚገባው መጠን መፍታት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት ብለዋል።

ለዚህም በሁሉም እርከኖች ያሉ የመንግስት አስተዳደር ሃላፊዎች እና ሰራተኞች በባለሃብቱ የሚነሱ ቅሬታዎችን በፍጥነት መፍታት የሚያስችል የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ፍሰትን ለማሳደግ በሀገር ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር ባሻገር ውጭ ባሉ ሚስዮኖችም የተጠናከረ የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.