Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትትሪ ቢሮ በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ5 ቢሊየን 735 ሚሊየን 633ሺህ በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጥቷል።

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብልጫ አለው ተብሏል።

ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ኮንስትራክሽን፣ ሆቴል፣ ቤት ልማት፣ ንግድ እና አገልግሎት ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎች መሆናቸው ተገልጿል።

የአልሚዎቹ ቁጥር 211 መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኢብራሂም አሕመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ ለ6 ሺህ 626 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል ብለዋል።

የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በይበልጥ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑም ተጠቁሟል።

የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በልማት ሥራዎች በንቃትእንዲሳተፉ ቢሮው በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ለማነቃቃት በጅግጅጋ ከተማ በ11 ሔክታር ላይ የኢንዱስትሪ መንደር መዘጋጀቱንም ነው አቶ ኢብራሂም የተናገሩት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.