Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአውሮፓ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በአውሮፓ ያደረጉትን የተሳካ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአውሮፓ ቆይታቸው ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በፓሪስ ተወያይተዋል፡፡

በውይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየጠነከረ ሲሄድ፥ ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንደሚሸጋገር እምነታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ልዑካቸው ከማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ቱሪዝም፣ በባሕር፣ በሎጅስቲክስ እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ማሳደግን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋርም በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የ180 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የያዘውን የ2023-2025 የኢትዮጵያ እና የጣልያን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፋይናንስ ስምምነቱ በኢኮኖሚ ልማት በተለይ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች፣ በጤና እና በትምህርት መሠረታዊ አገልግሎት አቅርቦት፣ ቁልፍ በሆኑ ተግባራት ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.