Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ከፈረንሳይ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ ከፈረንሳይ መንግስት ግምጃ ቤት የበላይ ሀላፊ ኢማኑኤል ሞሊን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስተር ዴዔታው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ ካደረጉት የስራ ጉብኝት በተጓዳኝ ከፈረንሳይ ግምጃ ቤት ሀላፊ ኢማኑኤል ሞሊን ጋር በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚዊ ትብብር ዙሪያ ፍሪያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በውይይታቸው ወቅት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች እያከናወነች ስላለችው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አብራርተዋል።

በግጭትና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን መልሶ የማቋቋሙ ሂደቱ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ ፈረንሳይ በሁለትዮሽና በብዙሀን የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው የልማት ድጋፍ ላይ አተኩሮ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈረንሳይ በበለጸጉት 20 ሀገራት ማዕቀፍ መሰረት የኢትዮጵያ የብድር ጫና የሚቃለልበትን ሂደት ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆኗ በውይይቱ መመላከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.