Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 6ወራት በሰላምና ልማት የተገኙ ስኬቶች እንዲጠናከሩ በትኩረት ይሠራል -አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ በግማሽ ዓመቱ ሰላምንና ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሠራል አሉ፡፡

6ኛው የአፋር ክልል ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ በሠመራ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡

ባለፉት 6 ወራት በክልሉ በመልካም አስተዳደር፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማት መስክ የተከናወኑ ዓበይት ክንውኖችን አቶ አወል አርባ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ከአጎራባች አማራና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያጋጥሙ የነበሩ ግጭቶችን በማስቀረት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ከሰሜኑ ኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ የተገኘው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ብለዋል አቶ አወል በሪፖርታቸው፡፡

ለዚህም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችና የማህበረሰብ መሪዎች የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚ ልማት መስክም ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

የሌማት ቱርፋትን ሥራዎችን ከማሳለጥ በተጨማሪ÷ በስንዴልማት፣ በእንስሳት፣ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተሠሩ ሥራዎች የሚበረታቱ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ማዕድን፣ ንግድና ገበያ ልማት ጨምሮ በተለያዩ የኢኮኖሚ ልማት መስኮች አበረታች ስኬት መገኘቱም ተገልጿል፡፡

በሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ድጋፍ እየቀረበ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.