Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን በተመለከተ በቅንጅት ለመሥራት ተስማምተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ወቅታዊ እና ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ፊሊፖ ግራንዲ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የስደተኞች አያያዝ አድንቀው ድጋፉ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።

አቶ ደመቀ በ2023 የዓለም አቀፍ የስደተኞች ፎረም ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ቀርቦላቸዋል መባሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.