Fana: At a Speed of Life!

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ከሃላፊነት አነሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኦትማን ጀራንዲን ከሃላፊነት አነሱ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአውሮፓ ህብረት የቱኒዚያ አምባሳደር  የሆኑትን ናቢል አማርን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት  መሾማቸው ነው የተገለፀው፡፡

ተሰናባቹ ዲፕሎማት  ጄራንዲ በፈረንጆቹ 2020 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን÷አሁን ላይ ከሃላፊነት የተነሱበት ምክንያት አለመገለጹ ተመላክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከንግድ፣ ከግብርና እና ከትምህርት ሚኒስትሮች በመቀጠል በፕሬዚዳንት ካይስ የተሰናበቱ አራተኛ ሚኒስትር መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የቱኒዚው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ በፕሬዚዳንትነት ሃላፊነታቸው ከፓርላማው ውሳኔ ውጭ  በፈረንጆቹ 2021 በሚኒስትሮች ላይ ተከታታይ እርምጃዎችን እየወሰዱ  ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፕሬዚዳንቱ  የፓርላማውን ስልጣን ችላ በማለት ለራሳቸው ያልተገደበ የአስፈጻሚነት ስልጣን ወስደዋል ሲሉ መክሰሳቸው ተሰምቷል፡፡

ቱኒዚያውያን በሀገሪቱ ባለው የኢኮኖሚው ሁኔታ እና በፕሬዚዳንቱ ያልተገደበ ስልጣን ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን÷ ቱኒዚያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የከፋ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያጋጠማት ነው ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.