Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሺህ ማለፉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ እና በሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ11 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል።

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ዛሬ እንደገለፁት÷ በቱርክ ቢያንስ 8 ሺህ 574 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በሶሪያ ደግሞ በአደጋው ሳቢያ ቢያንስ 2 ሺህ 530 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንቱ በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን፥ በ10 ግዛቶች ለሶስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡

የእርዳታ ሰጪ ተቋማት በጦርነት ለተጎዳችው ሶሪያ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታን ለመላክ ብርቱ ጥረት እያደረጉ መሆኑንም የአልጄዚራ ዘገባ ጠቁሟል፡፡

ከ12 ሺህ በላይ የቱርክ የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ9 ሺህ ወታደሮች ጋር በመሆን በተጎዱ አካባቢዎች የነፍስ አድን ስራ እየሰሩ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም ከ70 በላይ ሀገራት የነፍስ አድን ቡድኖችን እና ሌሎች እርዳታዎችን ማቅረባቸው ነው የተሰማው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.