Fana: At a Speed of Life!

የፀማይ ህዝብ የዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀማይ ህዝብ የዘመን መለወጫ የ‘ባርባይሳ’ ክብረ በዓል በደቡብ ኦሞ ዞን በበና ፀማይ ወረዳ ሉቃ ቀበሌ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የፀማይ ህዝብ የዘመን መለወጫ ‘ባርባይሳ’ በየዓመቱ የካቲት 1 ቀን በተለያዩ ባህላዊ ስነስርአቶች ይከበራል።

በክብረ በዓሉ ላይ የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የክልሉ ሴቶች ሊግ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ወላይቴ ቢቶ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳን ጨምሮ የዞኑ አመራሮች፣ የባህል መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የፀማይ ህዝብ አባላትም በዓሉን ታድመዋል።

የ‘ባርባይሳ’ በዓል የዘር እህል ተባርኮ የሚሰጥበትና የበልግ እርሻ ዘር የሚዘራበት እንዲሁም አካባቢው ሰላም እንዲሆን፣ ቂምና ቁርሾ እንዲወገድ ለፈጣሪ ጸሎትና ምስጋና የሚደረግበት መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም በሽታ ከሀገር እንዲጠፋ፣ ጎተራ እንዲሞላና ከብቶች ጋጣ እንዲሞሉ የሚመረቅበትና ወደ ፈጣሪ ተማፅኖ የሚደረግበት ክብረ በዓል እንደሆነም ተገልጿል።

በዓሉ በህዝቦች ዘንድ ሰላምና አንድነት እንዲሁም ተስፋና ልምላሜን በማሳየት ለበለጠ ውጤታማነት መነሳሳትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ባህላዊ ክንዋኔዎች የሚታዩበት እንደሆነም በስነ ስርአቱ ላይ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.