Fana: At a Speed of Life!

መዲናዋን ለአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው ወር አጋማሽ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ ሕብረት 36ተኛ መደበኛ ጉባዔ አስመልክቶ የብሄራዊ ዝግጅት ኮሚቴ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ጎበኘ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዋና ሹም ለአምባሳደር ደመቀ አጥናፉ÷ እስካሁን ያሉ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተሟላ ደረጃ እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

መሪዎች እና ተወካዮች በመዲናዋ የሚኖራቸውን ቆይታ ስኬታማ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርበት እየተሠራ ነው ማለታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበት አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበሩ÷ ከተማዋ ለእንግዶች ምቹ ለማድረግ በከተማ ደረጃ በተዋቀረው ኮሚቴ አስተባባሪነት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

እስካሁን ከተከናወኑ ተግባራት መካከልም÷የከተማ ፅዳት፣ የመንገድ ስርዓት አመልካች መገልገያዎችን ማስተካከል፣ የመብራት እና የውሃ አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም በአንዳንድ አካፋይ መንገዶች ላይ የማስዋብ እና መልሶ የማደስ ስራዎች የሚሉት ይገኙበታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.