Fana: At a Speed of Life!

ከፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመው የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋራ ግብረኃይሉ በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚሰራጩ ዘገባዎችና በመረጃ ስምሪቱ ባሰባሰባቸው ግብዓቶች መሠረት በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ
የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አካሄድ ክስተቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅተው ሀገራችንን ለማፍረስለሚሰሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በር እየከፈተ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝብና የዕምነቱ ተከታዮች ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ የጋራ ግብረ-ኃይሉ አመልክቷል።

ትናንት ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በሀገራችን እንገነባለን ስንል “እኛ ካልፈቀድንላችሁ በስተቀርመገንባት አትችሉም” ሲሉን የነበሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ዛሬ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ በመግባትአለመግባባቱን ለማባባስ ጊዜ አልወሰደባቸውም ያለው የጋራ ግብረ–ኃይሉ÷ እነዚህ የውጭ አካላት በቅርቡበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ እድል በመጠቀምልዩነትን የሚያጎላ እና ችግሩን የሚያባብስ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘታቸውን የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

ስለሆነም መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ የዕምነቱ አባቶችና የዕምነቱ ተከታዮች ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከውስጥየሽብር ኃይሎች ጋር እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ አንቂ ስም ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አና በአቋራጭስልጣን ለመያዝ ከሚሹ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅተው ሀገራችንን ወደማያባራ ብጥብጥለማስገባት እያደረጉ ያሉትን ቅስቀሳና እንቅስቃሴ በውል ተገንዝባችሁ የእኩይ ዓላማቸው ማስፈፀሚያእንዳትሆኑ የጋራ ግብረ-ኃይሉ በአጽንኦት አሳስቧል።

በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ የሕገወጥ ሰልፎቹ ቅስቀሳዎች የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀምናበህቡዕ በመደራጀት የአፍሪካ ሕብረትን ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማካሄድ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ከሚገኝበት ወቅት ጋር እንዲገጣጠሙ በማድረግ በሀገሪቱ የደኅንነት ስጋት እንዳለ በማስመሰል ጉባኤውእንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ በዕቅድ እየተመራ መሆኑን የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይሉ ደርሶበታል።

ሕገወጥ እንቅስቃሴዎቹ ደም አፋሳሽ እንዲሆኑ ታቅዶ ችግሩ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎችበርካታ የጦር መሣሪያዎች ሲዘዋወሩ የነበሩ ሲሆን÷ ግብረ –ኃይሉ ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሸን ከአዘዋዋሪ የደም ነጋዴ እንዲሁም ሽብርተኞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ይገልፃል።

በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ
ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን እንዲጠብቅ የጋራ ግብረ–ኃይሉ ያስጠነቀቀ ሲሆን÷
መላው ሕዝብ፣ የዕምነቱ ባቶችና ተከታዮች ለሀገራችን ሰላምና ደኅንነት እንደወትሮ ዘብ በመቆም
ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል ጋር ተቀናጅታችሁ እንድትሠሩ እና ማንኛውም አለመግባባት
በሠላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪውን ያቀርባል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ መሆናቸውን በማሳሳብ ግብረ – ኃይሉ ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ እንደሚወስድ ከወዲሁ በጥብቅ ያሳውቃል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ ለቤተክርስቲያኗ አባቶች እና ለዕምነቱ ተከታዮች የሚደረገውን የደኅንነት ጥበቃ ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ እንደሚቀጥል ጠቁሟል:፡

በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ የጋራ ግብረ –ኃይሉ ያሳስባል።

በመጨረሻም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሀገራችንን ስላምና ደኅንነት ለማደፍረስ ዝግጅት ማድረግ በመጀመራቸው ኅብረተሰቡ እንደተለመደው ሁሉ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ከግብረ -ኃይሉ ጎን እንዲቆም በድጋሚ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል ጥሪውን ያቀርባል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል

የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.