Fana: At a Speed of Life!

2 ነጥብ 7 ሚሊየን መጻሕፍት ተሰራጭቷል- የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እየተተገበረ ላለው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን መጻሕፍት ማሰራጨቱን አስታወቀ፡፡

ካለፈው በተሻለ ሁኔታ ለሁለተኛው መንፈቀ ዓመት አቅርቦት መኖሩን የቢሮው ሕዝብ ግንኙነት እና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በ1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተተገበረ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግን በሙከራ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ ለማድረስ ከ31 ሚሊየን 668 ሺህ 812 በላይ መጻሕፍት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

መጻሕፍቱን በአንድ ጊዜ ለማሳተም ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ ቢያንስ አንድ መፅሐፍ ለሦስት ተማሪዎች እንዲሆን እና በዙር እንዲታተም አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራ ነው ብለዋል ኃላፊው፡፡

ከ5 ሚሊየን በላይ መጻሕፍት በውጭ ሀገር የታተሙ ቢኖሩም በውጭ ምንዛሬ እጥረት መረከብ እንዳልተቻለም ነው የተናገሩት፡፡

የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በውጭ ሀገር ከታተሙት 8 ሚሊየን 888 ሺህ 169 መጻሕፍት ውስጥ እስካሁን 1 ሚሊየን 425 ሺህ 502 መጻሕፍት መሰራጨታቸውንም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የታተሙ 944 ሺህ 882 መጻሕፍት መሠራጨታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.