Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ እየቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቆላማ አካባቢዎች ባለፈው በልግ ወቅት በዝናብ እጥረት እና በግጭት ምክንያት ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጋንታ ጋምአ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በፌደራል መንግሥት፣ በክልሉ መንግሥት፣ በረጂ ድርጅቶች እና በህብረተሰቡ አማካኝነት ነው ድጋፉ እየቀረበ የሚገኘው።

ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ኮንሶ ዞን፣ የጎፋ ዞን የተወሰኑ ቆላማ ወረዳዎች፣ የጋሞ ዞን ቆላማ ወረዳዎች፣ የወላይታ ዞን ቆላማ ወረዳዎች እንዲሁም በማዕከላዊ ዞኖች ላይ የስምጥ ሸለቆ ወረዳዎች ድጋፉ የሚያስልፈጋቸው ወገኖች የሚገኙባቸው አካባቢዎች መሆናቸውንም አስረድተዋል።

ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ917 ሺህ በላይ ሰዎች የሴፍቲኔት ተጠቃሚ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ይህም ከታኅሣሥ ወር በፊት ለችግር ተጋልጠው የነበሩ ወገኖችን ቁጥር እንደሚቀንሰው ጠቅሰው፥ ከላይ ለተገለጹት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችም በጥር ወር ከ372 ሚሊየን ብር በላይ መቅረቡን ተናግረዋል።

የደቡብ ኦሞን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች ለሚኖሩ 300 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች በረጅ ድርጅቶች በኩል የዕለት ዕርዳታ እየቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም በሌሎች ስምንት ወረዳዎች ለሚገኙ 175 ሺህ ወገኖች ደግሞ ለሁለት ወር ፍጆታ የሚውል 114 ሚሊየን ብር ቀርቧል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል በ48 ወረዳዎች ለሚገኙ ከ250 ሺህ በላይ እናቶችና ሕጻናት አልሚ ምግብ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሌሎች ተጋላጭ ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግም ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር እየተሠራ መሆኑን እና ክልሉም የእህል ግዥ እያከናወነ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.