Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል የባለሙያዎች ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል የባለሙያዎች ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ በቀጠናው ያለውን ተገማች እና ኢ-ተገማች የሰላም እና ፀጥታ ስጋቶችን የበለጠ መከላከል እና ማስቀረት የሚቻልበትን ቁመና ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ሊቀ መንበር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ እንዳሉት ውይይቱ ባለፈው ጥቅምት ወር በኬንያ ናይሮቢ ከተካሄደው የቀጠለ ነው ብለዋል፡፡

በውይይቱ የተቋሙን አቅም እና የማድረግ ችሎታ የሚያሳድጉ እና የሚያጎለብቱ ጥናቶች እና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉበትም ተናግረዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ብሎም የአህጉሪቱን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን እና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል የራሱ የፀጥታ ምክር ቤት እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

የፀጥታ ምክር ቤቱ በአባል ሃገራቱ ድጋፍ ጠንካራ ቁመና እንዲኖረው እና በየጊዜው እየተገናኘ እንደሚመክር ተገልጿል።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.