Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመቱ 708 ሺህ 157 ሜትሪክ ቶን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ቀርቧል- ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ ዓመቱ ለሦስት ዙር የሚያስፈልግ 1 ሚሊየን 78 ሺህ 369 ሜትሪክ ቶን የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ለማቅረብ ታቅዶ 708 ሺህ 157 ሜትሪክ ቶን መቅረቡን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት የዕቅዱን 66 በመቶ ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የምክክር ጉባዔ በድሬዳዋ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

ኮሚሽኑ በግማሽ ዓመቱ÷ በግጭት፣ በድርቅና በጎርፍ አደጋ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው 21 ሚሊየን 306 ሺህ 871 ወገኖች ለሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት በመለየት አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማከናወኑ ተገልጿል።

በመንግስት አቅም ለ9 ሚሊየን 905 ሺህ 19 ተጎጂ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱን  እና በአጋር አካላት 11 ሚሊየን 401 ሺህ 852 ለሚሆኑ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መደረጉን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለ ማርያም ተናግረዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ወገኖች ውስጥ ከ16 ሚሊየን በላይ ያህሉ በድርቅ ምክንያት ተጎጅ የሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡

4 ነጥብ 6 ሚሊየን ያህሉ ወገኖች ደግሞ በሰው -ሠራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉና በከፊል ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ አብራተዋል፡፡

በማህሌት ተክለ ብርሃን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.