Fana: At a Speed of Life!

“የሕዳሴ ግድብ ጉዞ” የሚል ስያሜ ያለው የጉዞ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለውን አጋርነት የማጠናከር እና ገቢ የማሰባሰብ ዓላማ ያለው “ሕዳሴ ግድብ ጉዞ” የተሰኘ የጉዞ መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውን መርሐ ግብር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ አድን በጎ አድራጎት ድርጅት በመተባበር እንዳዘጋጁት ተገልጿል።

የጉዞ ተሳታፊ የሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

ከአንድ ወር በላይ ይቆያል የተባለው “የሕዳሴ ግድብ ጉዞ” በ50 የክልል ከተሞችና ሌሎች ወረዳዎች እንደሚከናወን ተነግሯል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ÷ የግድቡ ግንባታ ኢትዮጵያውያን ተባብረን መገደብ እንደጀመርነው ድጋፋችንንም አጠናክረን መቀጠል ይገባናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታሪክ ባህል እና ቅርስ አድን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አምሀ አለሙ በበኩላቸው፥ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ በሚካሄደው ጉዞ በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮች እስከ 200 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.