Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የመጀመሪያውን የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ የግዥ ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የበካይ ጋዝ ልቀት ቅነሳ የግዥ ማዕቀፍ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራረመች።
 
ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በምስራቅ አፍሪካ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል።
 
በሥምምነቱ መሰረት ውጤት ተኮር ለሆነ ደን ክብካቤና ጥበቃን ጨምሮ ተስማሚ የመሬት አጠቃቀሞችን በመተግበር የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚያግዝ እስከ 40 ሚሊየን የሚደርስ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ይደረጋል ነው የተባለው።
 
ሥምምነቱ የደን መመናመንን በመቀነስ እና ውጤታማ የደን ልማትና ክብካቤ በማድረግ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.