Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 2ኛው ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት አውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 2ኛው ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት አውደ ርዕይና ሲምፖዚየም በኤግዚቪሽን ማዕከል በይፋ ተጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ÷ የህብረት ስራ ማህበራትን ማጠናከር ህብረተሰቡን መደገፍ ነው ብለዋል፡፡

2ኛውን ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት አውደ ርዕይና ሲምፖዚየም በይፋ ማስጀመራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በከተማዋ  ፍትሀዊ  የግብይት ስርዓት እንዲኖር በማድረግ ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት ጫናን በማቃለል፣ ለህብረተሰቡ ምርትንና ሸቀጥን በየአካባቢው በእሁድ ገበያ እና በሸማች ሱቆች ተደራሽ በማድረግ ረገድ ማህበራት የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.